Mematsené Testo

Testo Mematsené

ቀና አታርጉኝ እኔን
ከሄደች ትታው መማፀኔን
ተክዤ ልግፋው ይሄ ሀዘኔን
ጨለማ አልብሳው ስትሄድ
የፈካው ቀኔን

እኔስ አቅም የለኝም
እባክሽ ብዬ ልመልሳት
ቢፈጀው ልቤን የፍቅር እሳት
አይሞከርም መቼም
እሷን ለመርሳት

ስትሄድ ስለያት ዛሬ ስሰናበታት
ማን አወቀልኝ ውስጤን እንደምወዳት
ልሸኛት እንጂ የሆዴን ችዬ
ባይል ነው ከላይ ግድ የለም ብዬ

ገና በጊዜ በቀዬው
አድባር አብረን አድገን
ክፋት በሌለው
በንፁ ፍቅር ተፈላልገን

ተዋደን ኖረን
ባልነበር ዓይነት በሚያስቀና
ልቧን ከልቤ
ድንገት ለያየው ቀን መጣና

በደለኛ ሰው
ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ
ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ
ሳይገባኝ ለኔ
የቱጋ እንደሆን እንኳ ማስቀየሜ
ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ

መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ
ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ
ታድያ እንዴት ይሆን
ወዳጅን መክሮ
ልብን መመለስ ወደ ድሮ

መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ
ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ
ታድያ እንዴት ይሆን
ወዳጅን መክሮ
ልብን መመለስ ወደ ድሮ

ቀና አታርጉኝ እኔን
ከሄደች ትታው መማፀኔን
ተክዤ ልግፋው ይሄ ሀዘኔን
ጨለማ አልብሳው ስትሄድ
የፈካው ቀኔን

እኔስ አቅም የለኝም
እባክሽ ብዬ ልመልሳት
ቢፈጀው ልቤን የፍቅር እሳት
አይሞከርም መቼም
እሷን ለመርሳት

ስትሄድ ስለያት ዛሬ ስሰናበታት
ማን አወቀልኝ ውስጤን እንደምወዳት
ልሸኛት እንጂ የሆዴን ችዬ
ባይል ነው ከላይ ግድ የለም ብዬ

በዚያ በሚዛን
ነፍስ ያለፍቅር መች ይሞላል
በሌለሽበት
ሲኖር ያላንቺ ቀን ይጎላል

እስኪ አውቀንበት
ሰው ሳንፈልግ ሌላ ዳኛ
ብለን ለፍቅር
ተይ እንገናኝ ዞረን እኛ

በደለኛ ሰው
ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ
ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ

ሳይገባኝ ለኔ
የቱጋ እንደሆን እንኳ ማስቀየሜ
ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ

መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ
ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ
ታድያ እንዴት ይሆን
ወዳጅን መክሮ
ልብን መመለስ ወደ ድሮ

መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ
ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ
ታድያ እንዴት ይሆን
ወዳጅን መክሮ
ልብን መመለስ ወደ ድሮ